1.
እግዚአብሔር ትወደዋለህ ? አዎ?
እግዚአብሔርን ትወደዋለህ ብለው
ሲጠይቁት በልብ ሙሉነት አዎ እግዚአብሔርን እወደዋለሁ ብየ ከመለስኩ
በሗላ ጥያቄውን እራሴን ደግሜ ብጠይቀው። አዎ ብሎ ለመመለስ የሚያስችል ድፍረት እንደሌለኝ ውስጤ ነገረኝ።እግዚአብሔርን ብወደውማ
ኑሮ፦
-
የእርሱን ህግጋት በአከበርኩ ነበር
-
ከራሴ ፈቃድ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በአስቀደምኩ ነበር
-
ጠላቶቼን በወደደኩ፣የራሴን የባንክ አካውንት ከፍ ለማድረግ ከመታገል ይልቅ
የተራቡትን ለማብላት የታረዙትን ለማስበስ በተጋሁ ነበር።
-
በክርስቶስ አምሳል የተሰራው ወንድሜ (እህቴ) በረሃብና ቁር እየተሰቃየ
በተዋቡ አልጋዎች ባልተኛሁ ነበር።……አረ ስንቱ!
እንደው እግዚአብሔርን አልወደውም ማለት ለአፌ ስለከበደው ነው እንጂ የምሰራው ስራ ግን ለእርሱ ያለኝን
ከምገልጥበት መንገድ የወጣ ሆኖ አስፈራኝ።
2. ከአንተና ከይሁዳ
ማን ይሻላል? እኔ ነኛ!
ይሁዳ እንኳ ጌታውን በሰላሳ ብር አሳልፎ የሸጠ
ነው አልኩት። ግን አሁንም እራሴን እና ጎደኞቼን አካባቢየን አለፍም ብየ የተለያዩ ሐገራት ያየሗቸውን ሳስተውል ስማችን በመፅሀፍ
ቅዱስ ስላልተመዘገበ እንጂ በዚህ ዘመንም በጣም ብዙ ይሁዳዎች አለን።
ይሁዳ ጌታን ከሁለት ሺ ዓመት በፊት ነው፡ በ ሳላሳ ብር የሸጠው ከ ሁለት ሺ ዓመት በፊት ደግሞ ሰላሳ ብር ምን ያህል ዋጋ ያለው
ብር እንደነበር መገመት አያደጋግተንም። ታዲያ በዚህ ዘመን ስንቶቻችን አይደለም በሰላሳ ብር ከዛ ባነሰ ዋጋ ጌታን ሸጠነዋል። እንኳን
ብር ተቀብለን ብር ከፍለን አይደለም እንዴ። ጌታን ከሚቃወሙት (ከዲያቢሎስ) ጭፍራዎች ጋር ማህበር የመሰረትነው። ብርከፍለን አይደለም
እንዴ ጠንቋይ ቤት ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰው ስለእኔ ያውቃል ብለን የምንሄደው። ብር ከፍለን አይደለም እንዴ ቤተ መቅደስ የሆነ
ሰውነታችንን በዝሙት ያረከስነው፡ ብዙ ገንዘብ እየከፈልን ከእግዚአብሔር
መንገድ የወጣንባቸውን ጉዳዮች ቤት ይቁጠረው። ታዲያ እኔ ከይሁዳ በምን እሻላለሁ? አልሻልም።
it is nice, keep it up
ReplyDelete